Press Release

ጋዜጣዊ መግለጫ

ፊርማ ሚዲያ፤ በኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ የፈጠራ መስክ ውስጥ የተሰማሩ “እጹብ” ግለሰቦች እና ድርጅቶችን እውቅና ለመስጠት እና ለማክበር በልዩ ሁኔታ የተዘጋጀውን የ2023 የነጋሪት አዋርድስ በይፋ መመሥረቱን ሲያበስር በታላቅ ኩራት ነው። በማስታወቂያ፣ በንድፍ ጥበብ እና በመረጃ /ግንኙነት መስክ የመጀመሪያ የሆነው ይህ ዝግጅት ከዚህ ቀደም ባልታየ መልኩ ወደር የለሽ የፈጠራ እና የአፈጻጸም ብቃትን በመጨመር በኢንዱስትሪው ላይ አዲስ ጮራን ለመፈንጠቅ ትልቅ ተነሳሽነት ያነገበ መድረክ ነው።

በሀገራችን በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነው ነጋሪት አዋርድስ፤ አዕምሯዊ ልህቀት ያላቸው ፈጠራዎችና የረቀቁ የኪነት ውጤቶች በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ የተለያዩ የብዙኀን መገናኛ መድረኮች ላይ ተደራሽ እንዲሆኑና እውቅናን እንዲያገኙ የሚያስችል የብርሃን ማማ ሆኖ ለማገልገል ያለመ ነው። ተልእኳችን የላቁ የፈጠራ ውጤቶችን እውቅና መስጠት ብቻ ሳይሆን በፈጠራ ባለሞያዎች ውስጥ ተነሳሽነትንና እና ትልልቅ ህልሞችን በመቀስቀስ፤ አዳዲስ የስኬት እርከኖችን እንዲያስመዘግቡ እና ለሀገራችን አወንታዊ የለውጥ ጉዞ ጉልህ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ማስቻልም ጭምር ነው።

ይህ ፕሮግራም ትልቅ የእውቅና መድረክን በማዘጋጀት፣ ትምህርት – ተኮር እንቅስቃሴዎችን እና እድገትን፣ ፈጠራን፣ እንዲሁም የትብብር ሥራዎችን ለማበረታታት የተነደፉ ትልልቅ የግንኙነት እድሎችን ለብዙኀኑ ዐይንና ጆሮ በማብቃት በኢትዮጵያውያን የፈጠራ ባህል ላይ እመርታዊ ለውጥ ለማምጣት ይጥራል።


ዘርፎች እና መስፈርቶች

ለ2023 የሽልማት ሥነ ስርዓት በጥንቃቄ የተመረጡትን ይፋዊ ዘርፎች ስናሳውቅ ከፍተኛ ደስታ ይሰማናል። የንድፍ ጥበብን፣ ዘመቻን፣ የፎቶግራፍ ጥበብን እና “የህይወት ዘመን ተሸላሚ”ን ጨምሮ የሚያካትቱት አሥሩ ዋና ዋና ዘርፎች መጠነ ሰፊ የሆኑ የፈጠራ ዘርፎችን የያዙ ሲሆን፤ እነዚህም አስራ ዘጠኝ ወደሚሆኑ ንዑስ ዘርፎች ተከፋፍለው፤ የተለያዩ ባለሙያዎች የተካኑባቸውን ብዛት ያላቸው የግል ሥራዎች አካትተው ያቀርባሉ።


የተከበረው የዳኞች ኮሚቴ (ስብስብ)

ታማኝነትን ለመጠበቅ እና በዳኝነት ሂደት ውስጥ ከፍተኛ የአስተውሎት ደረጃን ለመጨመር፤ እያንዳንዳቸው በፈጠራው ዘርፍ ከአሥር ዓመታት በላይ ልምድ ባላቸው ሠላሳ የተከበሩ የኢንዱስትሪው ባለሙያዎች የተዋቀረ ኮሚቴ አቋቁመናል። እነዚህ የተከበሩ ዳኞች የዚህ ወሳኝ ዝግጅት አካል ለመሆን ያሳዩት ቁርጠኝነት በኢትዮጵያ የፈጠራ ባህልን ከፍ ለማድረግ፣ እንዲሁም አዳዲስ ግኝቶችን እና የልህቀት ሙከራዎችን ለማዳበር ካለን የጋራ ራዕይ ጋር እጅና ጓንት ሆኖ የሚሄድ ነው። የግምገማ ሂደቱ የሚጀመረው የማስረከብያ ቀነ ገደብ ከተጠናቀቀ በኋላ ሲሆን ሂደቱም አንድ ወር ይወስዳል።


ግምገማ እና የእውቅና አሰጣጥ

ለውድድሩ የሚቀርቡ ሥራዎች፤ ልዩ መሆንን፣ አዲስነትን፣ የአፈጻጸም ልህቀትን እና የፈጠራ ሥራዎቹ የታለሙላቸውን አላማዎች በማሳካት በኩል ያላቸውን ውጤታማነት ጨምሮ ሌሎች ለላቀ የፈጠራ ሥራ ወሳኝ የሆኑ መስፈርቶችን መሠረት በማድረግ በጥንቃቄ ይገመገማሉ። አደጋን መጋፈጥን፣ ትልልቅ ሀሳቦችን ማሰስን፣ አዲስ ዓይነት የታሪክ ነገራ ችሎታን እና ስሜታዊ ግብረ መልሶችን የመቀስቀስ ችሎታን ለሚያሳዩ ተወዳዳሪዎች ልዩ የእውቅና ሥነ ስርዓት ይካሄዳል።


ሽልማቶችና እውቅናዎች

በተለያዩ ዘርፎች ልህቀት ላሳዩ ሥራዎች 21 የዘርፍ ሽልማቶች፤ እንዲሁም የኪነ-ጥበባዊ ስኬት ተምሳሌትነቱን የሚወክል እና የተሸላሚውን የምርት ወይም የአገልግሎት ስም ክብር የሚያሳድግ አንድ የህይወት ዘመን ሽልማት የሚሰጡ ይሆናል። ከዚህም በተጨማሪ፣ በእጩነት የቀረቡ እና ወደር በሌለው ሥራቸው ዕውቅና የተሰጣቸው ተወዳዳሪዎች በነጋሪት አዋርድስ ገጸ-ድር ላይ በልዩ ሁኔታ ይቀርባሉ።

በኢትዮጵያ ውስጥ ኪነ-ጥበብ እና ፈጠራ ያላቸውን የለውጥ ኃይል እውቅና በመስጠትና እና በማድነቅ አገራዊውን የፈጠራ ሜዳ ታይቶ በማይታወቅ መጠን ለማስፋት አንድ ላይ በመሰባሰባችን ሀሴት እናደርጋለን። ፊርማ ሚዲያ በነጋሪት አዋርድስ አማካኝነት ለፈጠራው ማህበረሰብ መዳበር የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማበርከት ከፍተኛ ቁርጠኝነት ያለው ሲሆን በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚደረገው ለፈጠራ ልህቀት እውቅና የመስጠት እና የማክበር ሂደት ወሳኝ ሚና በመጫወቱ እጅግ ደስተኛ ነው። ይህ ዝግጅት በሀገራችን ፈጠራዊ ግኝቶችን እና ልህቀትን በማጎልበት ረገድ የሚኖረውን ዘላቂ ተጽእኖ ለማየት ባለ ሙሉ ተስፋዎች ነን።
FORMAL PRESS RELEASE

FIRMA Media Introduces the Inaugural 2023 Negarit Awards

FIRMA Media is honored to formally announce the inaugural 2023 Negarit Awards ceremony, a landmark event meticulously designed to acknowledge and celebrate remarkable individuals and organizations within Ethiopia’s dynamic creative sector. This groundbreaking event is a first in the realm of advertising, design, and communications in Ethiopia, marking a pivotal initiative to shine a light on unparalleled creativity and outstanding execution within the industry.

The Negarit Awards, being the first of its kind in the nation, aim to serve as a lighthouse of recognition for creative brilliance and sophisticated artistry across a multitude of media platforms within Ethiopia. Our mission is to not only recognize excellence in creativity but also to foster inspiration and aspiration among creative professionals, encouraging them to scale new pinnacles of achievement and contribute significantly to the nation’s positive evolution.

This initiative endeavors to bring transformative change to the Ethiopian creative landscape by providing robust recognition, enlightening educational endeavors, and prolific networking opportunities designed to spur growth, innovation, and collaborative ventures.


Categories and Criteria

We are pleased to present the meticulously defined official categories for the 2023 awards ceremony . The ten principal categories, encompassing Design, Campaign, Photography, and Agency of the Y ear , among others, span across a broad spectrum of creative domains, and are further refined into nineteen sub-categories, assuring inclusivity of a vast range of specializations.


Esteemed Judging Panel

To uphold impeccable integrity and ensure a high standard of expertise in the adjudication process, we have convened a panel of thirty esteemed industry veterans, each possessing over a decade of experience in the creative sphere. The commitment from such revered judges to be part of this groundbreaking endeavor resonates with the shared vision to elevate the creative standards and foster a culture of innovation and excellence within Ethiopia. The evaluation process will commence and continue for the duration of one month after the application submission period concludes.


Evaluation and Recognition

Entries will be scrupulously assessed based on elements crucial to superior creative work, including uniqueness, originality, executional excellence, and the effectiveness of the creative piece in meeting its intended objectives. Special commendation will be accorded to submissions showcasing risk-taking, exploration of novel ideas, technical storytelling prowess, and the ability to provoke emotional responses.


Awards and Honors

In salutation of exceptional work across various categories, twenty-one category trophies will be conferred, along with a singular distinguished lifetime achievement award, symbolizing the epitome of artistic accomplishment and enhancing the prestige of the affiliated brand. Moreover , the nominated entries, recognized for their unparalleled work, will be prominently featured on the illustrious Negarit Awards website.

We are excited to come together to honor and acclaim the transformative power of creativity and artistry in Ethiopia and elevate the national creative landscape to unprecedented heights. FIRMA Media is deeply committed to contributing to the enrichment of the creative community through the Negarit Awards and is excited to play a pivotal role in recognizing and celebrating creative excellence in Ethiopia for the first time. We look forward to witnessing the lasting impact this initiative will have on fostering creative innovation and excellence in the nation.